አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን በቱርክ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የኢትዮጵያ መንግስት ላደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ለተደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ በቱርክ ለኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሃመድ እና የኢትዮጵያ የነፍስ አድን ልዑካንን ለመሩት ሌተናል ጀኔራል ደስታ አብቼ የፕሬዚዳንታዊ ሜዳሊያ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡
ባለፈው የካቲት ወር በቱርክ ከ59 ሺህ በላይ ዜጎችን ለህልፈት የዳረገ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከስቶ የነበረ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ የነፍስ አድን ልዑካንም በቱርክ የሰብዓዊ እርዳታ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

