Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና የባለስልጣናት ቡድን መቀሌ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና የባለስልጣናት ቡድን ወደ መቀሌ ገብቷል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤና የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች መቀሌ ከገባው የባለስልጣናት ቡድን ውስጥ ይገኛሉ።

ርዕሳነ መስተዳድሮቹ እና ባለስልጣናቱ መቀሌ ሲደርሱም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

Exit mobile version