Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአቶ ግርማ የሺጥላ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቶ ግርማ የሺጥላ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በትውልድ ስፍራቸው ሰሜን ሸዋ ዞን መሃል ሜዳ ከተማ ተፈጽሟል፡፡

በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ  የአቶ ግርማ የሺጥላ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ባልደረቦች እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የአቶ ግርማ የሺጥላ አስከሬን ቤተሰቦቻቸው፣ የስራ ባልደረቦች፣ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ጠዋት በወዳጅነት አደባባይ አሸኛኘት ተደርጎለታል፡፡

አቶ ግርማ የሺጥላ ከመስከረም 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሕይወታቸውን በድንገተኛ አደጋ እስከተነጠቁበት ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ እና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።

አቶ ግርማ የሺጥላ ወ/ጻዲቅ ከእናታቸው ወ/ሮ ዘውዴ ስመኝ እና ከአባታቸው አቶ የሺጥላ ወ/ጻዲቅ በቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሃገር በመንዝና ግሼ አውራጃ በጌራ ምድር ወረዳ መሃል ሜዳ ከተማ በ1967 ዓ.ም ነበር የተወለዱት፡፡

አቶ ግርማ የሺጥላ ባለትዳር የሶስት ሴት እና የአራት ወንድ ልጆች አባት ነበሩ፡፡

Exit mobile version