Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የግብርና ኤግዚቢሽንን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግብርና ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የግብርና ኤግዚቢሽን በሳይንስ ሙዚየም መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ “ከቤተ ሙከራ ወደ አዝመራ” በሚል መሪ ቃል በግብርና ሚኒስቴር እና አጋር አካላት በጋራ በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የሳይንስና የግብርና ኤግዚቢሽን ነው መርቀው የከፈቱት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት “ያለን መሬት ላይ ምርታማነትን ማሣደግ” ይገባል።

ግብርናን ማዘመን ፍላጎትን ለማሟላት እንደሚያግዝ ጠቅሰው፥ “ያለን ሀብት ላይ እሴት በመጨመር ሀገርን እንዲጠቅም በየጊዜው ሥራችንን ማጎልበትና ማዘመንም አለብን” ነው ያሉት።

አሁን ላይ በግብርናው ዘርፍ እየታየ ያለው ለውጥ ተሥፋ ሰጭ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ኤግዚቢሽኑን ሁሉም አካል መጥቶ እንዲጎበኝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኤግዚቢሽኑም የተለያዩ የግብርና ምርቶችና ቴክኖሎጅዎች ለእይታ ቀርበዋል።

የአገሪቷ የግብርና አሰራር ስርዓት ያስቀመጠውን አሻራ እና በዲጂታል አብዮት የግብርናን ስራ አቅጣጫ ማሳየት የኤግዚቢሽኑ ግብ ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡

በግብርና ሳይንስ ኤግዚቢሽኑ መክፈቻ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉበኤ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስ የስራ ሀላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ኤግዚብሽኑ ከሚያዝያ 30 ጀምሮ ለተከታታይ ሳምንታት ለህዝብ እይታ ክፍት እንደሚሆንም ተገልጿል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ፣ ቃልአብ ግርማ እና ሰሎሞን ይታየው

Exit mobile version