Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካን ሃብቶችና ፀጋዎች ወደ ተጨባጭ የብልፅግና ዓቅም ለመቀየር የሰላምና ፀጥታ መረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካን አያሌ ሃብቶችና ፀጋዎች ወደ ተጨባጭ የብልፅግና ዓቅም ለመቀየር የአፍሪካ የሰላምና ፀጥታ መረጋገጥ ምትክ የሌለው ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አስታወቁ።

ለዚህም ሁሉም የጋራ ኃላፊነት እንዳለበት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል።

ከሁሉ በላቀ ደግሞ የአፍሪካ የመከላከያ አዛዦች፣ የሰላምና ፀጥታ አመራሮች ይህን ወሳኝ ሚና መጫወት አለባቸው ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version