Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ ከስዊድኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስቴፈን ሎቫን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስዊድኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስቴፈን ሎቫን ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም የኮቪድ19ን አስከፊ ውጤቶች ለመከላከል በሀገር እና በቀጠና ደረጃ ስለሚካሄዱ ጥረቶች መምከራቸውን በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

በዚህ ፈታኝ ወቅት እንዲህ ያሉ ዓለም አቀፍ የትብብር ሥራዎች አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

አያይዘውም የስዊድን መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር በአብሮነት መቆሙንም አድንቀዋል።

Exit mobile version