Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ የመጀመሪያ ምዕራፍ አፈጻጸም ላይና የሁለተኛው ምዕራፍ ዝግጅት ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ትናንት የመንግስት የ2015 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት አፈጻጸም መገምገሙ ይታወቃል።

እየተካሄደ ባለው ውይይት ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የተቋማት ኃላፊዎችና የሕዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

በዛሬው የግምገማ መድረክ ከ2012 እስከ 2015 ዓ.ም የተተገበረው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አፈጻጸምን በመዳሰስ በተዘጋጀው ሁለተኛው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ ምክክር ይደረጋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) ፥ መንግስት ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ የተቀዳውን የመጀመሪያው ምዕራፍ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሦስት ዓመታት በመተግበር በተለያዩ ጫናዎች ውስጥ ሆኖ ስኬት መመዝገቡን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ከሠሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት በአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት(ጂዲፒ) ሦስተኛ ደረጃ ላይ መሆኗን መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

አዳዲስ ተግዳሮቶችን መቋቋም የሚችል ኢኮኖሚን ለመገንባት ተጨማሪ የሀገራዊ የኢኮኖሚ ልማትና ብልፅግና ማስፈጸሚያ ተጨማሪ እቅድ በማስፈለጉ ሁለተኛ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version