Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቤጂንግ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቻይና ቤጂንግ ገባ።

ልዑኩ ቤጂንግ ሲደርስ በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች፣ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች እና በቻይና የዳይስፖራ ማህበረሰብ ተወካዮች አቀባበል ተደርጎለታል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ በቻይና ጉብኝት እንዲያደርጉ ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ነው ዛሬ ቤጂንግ የገቡት።

አቶ ደመቀ በቆይታቸው ከቻይና የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Exit mobile version