አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት የተመሰረተበት 60ኛ አመት በነገው እለት ይከበራል።
በፈረንጆቹ 1963 በ32 ነጻ ሀገራት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በሚል መመስረቱ ይታወሳል።
በአከባበሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳፋኪ ማሃማት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር አዛሊ አሱማኒ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ የህብረቱ መረጃ ያመላክታል።
እለቱ ለቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ ብሎም ለአህጉራዊው የማህበረ ኢኮኖሚ መነቃቃት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትን ለመዘከር እድል ይፈጥራል ተብሏል።