አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ቀን በኢትዮጵያ አዲስ አበባ እና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እየተከበረ ነው፡፡
የአፍሪካ ቀን የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት በፈረንጆቹ 1963 መመስረትን ተከትሎ ነው በየዓመቱ የሚከበረው፡፡
በፈረንጆቹ 1963 ከቅኝ ግዛት ነጻ የወጡ 32 ሀገራት የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በአዲስ አበባ መመስረታቸው ይታወሳል፡፡
የአፍሪካ ህብረት የተመሰረተበት 60ኛ ዓመትም በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ዛሬ በሚከናወነው የአፍሪካ ቀን አከባበር ስነ ስርዓትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳፋኪ ማሃማት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር አዛሊ አሱማኒ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል፡፡