Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ በጅቡቲ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች በጅቡቲ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

መሪዎቹ ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ መጠናቀቅ በኋላ ነው አረንጓዴ አሻራቸውን ያሳረፉት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷የኢጋድ አባል ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን አስከፊ ተጽዕኖዎች ያለማቋረጥ ተጋፍጠዋቸዋል ብለዋል።

በስኬት ከተጠናቀቀው የኢጋድ ስብሰባ በኋላም ከመሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በጅቡቲ ችግኝ መትከላቸውን አንስተዋል፡፡

Exit mobile version