Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካ ኢኖቬሽንና ዲጂታል ጉባዔ በኢትዮጵያ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው የአፍሪካ ኢኖቬሽንና ዲጂታል ጉባዔ “ዲጂታል አፍሪካ” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባዔው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና ከአፍሪካ ሀገራት የተወከሉ የዘርፉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት የተወጣጡ አካላት እየተሳተፉ ነው።

እንደሀገር ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፉ ትልቅ ትኩረት መሰጠቱን በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በጉባዔው ላይ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በመሰረተ ልማት ግንባታ፣ በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በጤናና ሌሎች ሴክተሮች በስፋት በመጠቀም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየተጋች መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባዔ የቴክኖሎጂ የልምድ ልውውጥ እንደሚደረግ ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version