አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኩዌት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ባድር ሳሌህ አል ቱናይብ ጋር መክረዋል፡፡
የሥራ ኃላፊዎቹ በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
አቶ ደመቀ በዚህ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ ከኩዌት ጋር ላላት ግንኙነት ልዩ ትኩረት እንደምትሰጥና በኩዌት ፈንድ በኩል የሚደረገውን የልማት ትብብርን እንደምታደንቅ ገልጸዋል።
የኩዌት ባለኃብቶች በሃይል አቅርቦት፣ በሎጅስቲክስና በግብርና ዘርፍ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጠይቀዋል።
የኩዌት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ባድር ሳሌህ አል ቱናይብ በበኩላቸው÷ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ጽኑ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።
ሁለቱ ባለስልጣናት የጋራ የሚኒስትሮች ምክክር ለማድረግ መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!