አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ ክልል ኮንሶ ሁለተኛውን ምዕራፍ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዛሬ አስጀምረዋል፡፡
“በእርከን ሥራ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በውኃ ማቆር እና በጥንታዊ የእጅ መሣሪያዎች በታወቀው የኮንሶ ሕዝብ መካከል በመገኘቴ እጅግ ደስ ብሎኛል” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እያንዳንዱን የሀገሪቱን ጥግ ለመሸፈን ያለመ ስለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ በደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቶም ወረዳ አረንጓዴ ዐሻራቸውን በማሳረፍ÷ ምዕራፍ ሁለት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ማስጀመራቸው ይታወቃል፡፡