Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የ2016 በጀት 801 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል መንግስት የ2016 በጀት 801 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸድቋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2016 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት ላይ የቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት በጀትን አስመልክቶ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 28ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት አካሂዷል፡፡

ምክር ቤቱ ባካሄደው 28ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የ2016 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 801 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር እንዲሆን የተያዘ ሲሆን÷ ከዚህም ውስጥ 203 ነጥብ 9 ቢሊየን ብሩ ለካፒታል በጀት ተመድቧል፡፡

369 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ለመደበኛ ወጪ፣ 214 ነጥብ 07 ቢሊየን ብሩ ደግሞ ለክልል መንግስታት ድጋፍ እንደሚከፋፈል ተገልጿል።

ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ደግሞ 14 ቢሊየን ብር የተመደበ ሲሆን÷ የፀደቀው በጀት ከ2015 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ15 ቢሊየን ብር ጭማሪ አለው ተብሏል።

Exit mobile version