Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዲጂታል ጤና የጤናው ዘርፍ ግቦችን ለማሳካት መልካም አጋጣሚዎችን እየፈጠረ ነው – ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዲጂታል ጤና በጤናው ዘርፍ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል መልካም አጋጣሚዎችን እየፈጠረ እንደሆነ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

 

ዲጂታል ጤና ሁሉ አቀፍ የጤና ሽፋንን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ከመደገፉም በላይ የጤና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እንደሚረዳም ተናግረዋል።

 

ጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል ከሆነው ከቤተር ዛን ካሽ አሊያንስ ጋር በመተባበር የዲጂታል ጤና ስርአቶችን ከዲጂታል ክፍያ ስርአት ጋር ለማስተሳሰር የሚረዳ የውይይት መድረክ አካሂደዋል።

 

በጤናው ሴክተር ውስጥ ለመጀመር የታሰበው የዲጂታል ክፍያ ስርአት የጤናውን ዘርፍ በሚደግፍበት ሁኔታ ላይ መድረኩ መምከሩን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

 

የዲጂታል ጤና ስርአት በጤናው ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በግልጽ የሚታይ ለውጥ ማምጣቱን የገለጹት ዶ/ር ሊያ፥ ከዲጂታል የክፍያ ስርአት ጋር ማስተሳሰር የጤና አገልግሎት በተቀላጠፈ መንገድ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

Exit mobile version