Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በተያዘው ዓመት 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተያዘው ዓመት 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን አስታወቁ።

የባለፈውን ዓመት ስኬት መነሻ በማድረቅ እቅዱ መዘጋጀቱን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ ኮቪድ19 ሥርጭትን ለመግታት እየተጋን፣ እንደ ሀገር አረንጓዴ ዐሻራ ማሳረፋችንን እንቀጥላለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በባለፈው ዓመት የክረምት ወቅት በኢትዮጵያ 4 ቢሊየን ችግኝ መተከሉ የሚታወስ ነው።

ከዚህ ባለፈ በአንድ ቀን 350 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያ የአለም ክብረወሰንን መስበሯ አይዘነጋም።

Exit mobile version