Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ባለፉት 24 ሰዓታት 1 ሺህ 560 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1 ሺህ 560 ሰዎችየ ላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት ቫይረሱ የተገኘባቸው የ49 ዓመት ወንድ እና የ45 ዓመት ሴት ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ከዚህ ውስጥ አንደኛው ከዝዋይ ወደ አዲስ አበባ መጥተው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ ያለ ሲሆኑ፥ የውጪ ሃገር ጉዞም ሆን በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ሳይኖራቸው ናሙናቸውም ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን የተወሰደ ነው።

ሁለተኛዋ ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰብ ደግሞ የስልጤ ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ በቤት ውስጥ ቅኝት እና አሰሳ የተለዩ ናቸው፡፡

አሁን ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 135 የደረሰ ሲሆን፥ 75 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል ነው የተባለው።

ከዚህ ውስጥ ስድስቱ ሰዎች አዲስ ያገገሙ መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version