Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን በርካታ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመረቁ፡፡

በዚህም ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 124 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 1ሺህ 835 በቅድመ-ምረቃ መርሀግብር ፣ 282 በድህረ ምርቃ መርሃ ግብር እና 7 በፒ.ኤች.ዲ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎች ናቸው፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ የትምህርት መርሃ-ግብሮች ያሰለጠናቸውን ከ1 ሺህ 829 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችን አስመርቋል ።

ዩኒቨርሲቲው የሚያስመርቀዉ ለ25ተኛ ጊዜ ሲሆን÷ ተማሪዎቹም በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ ድግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ መርሃ-ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ናቸው ።

እንዲሁም የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው እና በተከታታይ መርሐ ግብር በመጀመሪያ ፣ በሁለተኛ እና በሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

አምቦ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 4 ሺህ 36 ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው 2 ሺህ 829 በቅድመ ምረቃ 1 ሺህ 207 ደግሞ በድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ነው አስመርቋል፡

ከነዚህ ውስጥም 1 ሺህ 69ኙ ሴቶች መሆናቸውን በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

በህክምና ትምህርት እንዲሁ 21 ተማሪዎችን የሚያስመርቅ ሲሆን÷ ዩኒቨርሲቲው ለ2 ወንዶች እና ለአንድ ሴት የፒ ኤች ዲግሪም ይሰጣል።

በተጨማሪም የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በ 80 የተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 347 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ ውስጥም 1ሺህ76ቱ ወንዶች ሲሆኑ 271ዱ ሴቶች ናቸው ተብሏል።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲም በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 715 ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡

እንዲሁም የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በማስተርስ እና በዶክትሬት ዲግሪ ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው፡፡

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲም 1 ሺህ 90 ተማሪዎችን ነው አስመርቋል::

ከተመራቂዎቹ መካከል 268ቱ ሴቶች 820ቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል።

በተመሳሳይ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 299 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

በተመሳሳይም ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በተከታታይና ርቀት ትምህርት መርሐ ግብር በ37 ፕሮግራሞች በቅድመ እና በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 309 ተማሪዎችን አስመርቋል።

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 286 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በቅዳሜ እና እሁድ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል።

ደብረ ብርሃን ፣ጂንካ፣ወልቂጤ፣ቀብሪደሀር ፣ደብረ ታቦር ፣ደባርቅ፣አርባምንጭ እና መቱ ዩኒቨርሲዎችም በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በመደበኛውና በተከታታይ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል፡፡

በህይወት አበበ፣ጋለነ ተሰፈ፣ ጋሻው አርጋው ፣እየሩሳሌም አበበ፣ነስሪ ዩሱፍ እና ወርቅአፈራው ያለው ተጨማሪ መረጃ ከየዩኒቨርሲቲዎቹ

Exit mobile version