ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የ9 ወራት የስራ እቅድ አፈፃፀም ረፖርቱን ለተጠሪ ተቋማት አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የ9 ወራት የስራ እቅድ አፈፃፀም ረፖርት ተጠሪ ተቋማት እና ምድብ ፅህፈት ቤት ሃላፊዎች በተገኙበት በሸራትን አዲስ ሆቴል አቅርቧል።
በአሁኑ ወቅት ዋናው ርብርብ ኮቪድ-19 መከላከል ቢሆንም የተቋማቱ ሀላፊነት ለዜጎች የመብት እና የፍትህ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ጋር ተያይዞ ይህ ስብሰባ በልዩ ሁኔታ የተፈቀደ መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
ያንንም ተከትሎ የቀጣይ ጊዜ አቅጣጫ በተመለከተ መግባባት ላይ ይደረሳል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ ሴክተሩ በፍትህ ሂደቱ ላይ በማስፈፀም አቅሙ ዝቅተኛነት፣ ግልፀኝነት እና የሙያ ስነ ምግባር እና ቅንጅታዊ አሰራር ላይ ክፍተት ይታይበት ነበር ተብሏል።
ከለውጡ በኋላ ዘርፉ ያለበትን ክፍተት ለመሙላት እና የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውም በግምገማው ተነስቷል።
ለዚህም እንዲያመች አብዛኛው ሰራተኞቹን በፍትህ ሂደቱ ላይ እንዲሰሩ አድርጓል ነው የተባለው።
ነገር ግን አሁንም በተለይ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ፣ በዘርፉ ያሉትን ሙያተኞች ማብቃት እና የስራ ሂደቱን ቀልጣፋ ማድረግ ላይ ያለው ክፍተት አሁንም አለመቀረፉ ተነግሯል።
የወንጀል ጉዳዮችን በቶሎ ወደ ሚመለከታቸው አካላት ያለማድረስ እና የፍትህ አሰጣጥ ችግርም ሌላኛው ያልተፈታ ችግር ሆኖ ይታያል።
በአጠቃላይም ሴክተሩን አዘምኖ ዜጎች ሚፈልጉትን ምላሽ እንዲያገኙ ተቋሙ ከፍተኛ ስራዎች እንደሚጠበቁበትም በግምገማው ተነስቷል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።