Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ደመቀ መኮንን ለተመራቂ ተማሪዎች የአንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በዛሬው እለት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለተመረቁ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈዋል፡፡

አቶ ደመቀ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባተላለፉት መልዕክት÷ በመላው ሀገራችን በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የምረቃ በዓላቸውን ላካሄዱ እንዲሁም በዝግጅት ላይ ላሉ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እፈልጋለሁ ብለዋል::

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በዛሬው እለት የምረቃ በዓሉን ማካሄዱን ያነሱት አቶ ደመቀ ÷ ተማሪዎች ለምርቃት እንዲበቁ ጥረት ላድረጉ ወላጆች እና መምህራን እንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ተመራቂዎች በቀሪ ዘመናቸው ፍሬያማ ህይወት እንዲኖራቸው እና መልካም ነገር እንዲገጥማቸው መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

Exit mobile version