Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀምረዋል፡፡

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ከ11 ክፍለከተሞች የተውጣጡ የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኞች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ላይ ናቸው፡፡

በተጨማሪም ተፈታኞች ወደ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ የአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ፌደራል ቴክኒክና ስልጠና ኢንስቲትዩት እየገቡ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ደረጃ 24 ሺህ 775 የማኅበራዊ ሣይንስ ተማሪዎችፈተና ይወስዳሉ መባሉን የከተማዋ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞችን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን እየተቀበለ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በሁለቱም ዙር በሦስት ግቢዎች ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስፈትናል።

ፈተናው ከሐምሌ 19 እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

Exit mobile version