Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የእስራዔሉ ‘ሴቭ ዘ ቻይልድ ኸርት’ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተሥማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በእራኤል ሀገር ከሚገኘው ‘ሴቭ ዘ ቻይልድ ኸርት’ ጋር በሕፃናት የልብ ሕክምና አገልግሎት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸው ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለዓመታት ከተለያዩ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች እና ሀገራት ጋር በጋራ ሲሰራ ቆይቷል።

ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የእስራኤል ኤምባሲ ሲሆን ÷ ኤምባሲው ለልብ ሕክምና የሚያስፈልጉ እቃዎች ማሟላትን ጨምሮ የልብ ሕሙማን እስራኤል ሀገር ሄደው እንዲታከሙ እስከማድረግ የሚደርስ ስምምነት ከኮሌጁ ጋር መፈጸሙ ተመላክቷል።

በተጨማሪም የዕውቀት ሽግርርን ታሳቢ ያደረገ ሥራ እንደሚሰራ በኢትዮጵያ የእስራዔል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ተናግረዋል፡፡

አምባሳደሩ “በጋራ ከሠራን ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን ጭምር አገልግሎት የሚሰጡ ሐኪሞችን ማፍራት ትችላለች” ብለዋል።

ይህም የኢትዮጵያን እና የእራኤልን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ጠቅሰዋል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በኢትዮጵያ የእስራዔል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ፣ የሴቭ ዘ ቻይልድ ኸርት ኃላፊ ሳይመን ፊሽ ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር አንዷለም ደነቀ እንዲሁም የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የልብ ሐኪሞች ተገኝተዋል፡፡

በፈቲያ አብደላ

Exit mobile version