Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሰው ሀብት ለዘላቂ ልማት መግቢያ መንገድ ነው- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰው ሀብት ልማት ለዘላቂ ልማት መግቢያ መንገድ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በታንዛኒያ ዳሬሰላም እየተካሄደ ባለው “የአፍሪካ የሰው ሀብት ልማት የመሪዎች ጉባኤ” ላይ እየተሳተፈ ነው።

አቶ ደመቀ “በትምህርትና ምርታማነት ላይ በአፍሪካውያን ወጣቶች ላይ ለመስራት ዝግጁ ነን?” በሚል ርዕስ በትምህርት ላይ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ተሳትፈዋል።

በዚህ ወቅትም የሰው ሃብት ልማት ወደ ዘላቂ ልማት መግቢያ መንገድ እና አካታች እቅድና ፕሮግራሞችን ለመተግበር የሚረዳ መሳሪያ መሆኑን አንስተዋል።

በሰዎች ላይ መስራት ለመስራት ጊዜው አሁን ነው ያሉት አቶ ደመቀ አፍሪካውያን ለሰው ሃብት ልማት ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የአስር አመት የልማት እቅዱን ከሰው ሀብት ልማት ጋር ማጣጣሙን በመጥቀስ÷ ለዚህ ለትምህርቱ ዘርፍ ዋነኛ ትኩረት መስጠቱን አስምረውበታል።

ጥራት፣ ተደራሽ፣ ተመጣጣኝ እና ለሁሉም ዜጎች ተገቢነት ያለው ትምህርት ለመስጠት መንግስት ያለውን ቁርጠኝነትም አቶ ደመቀ አብራርተዋል።

ለዚህም ኢትዮጵያ ሃብትን በማሰባሰብ ከዓለም ባንክ፣ ከግሉ ዘርፍ እና ከሲቪክ ማህበራት እንዲሁም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ አጋሮች ጋር በቅርበት ለመስራት ትጥራለች ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version