Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከጅቡቲ ተጓጉዞ አዲስ አበባ የገባው የአፈር ማዳበሪያ በአስቸኳይ ለክልሎች እንዲሰራጭ ግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጅቡቲ ተጓጉዞ አዲስ አበባ የገባው የአፈር ማዳበሪያ በአስቸኳይ ለክልሎች እንዲሰራጭ ግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፍያ ካሳ (ዶ/ር) ሣሪስ አከባቢ በሚገኘው የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ድንገተኛ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝታቸውም ከ20 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሁለት ቀንና ከዛ በላይ አዲስ አበባ ገብተው ማዳበሪያ ሣያራግፉ መቆማቸውን ተመልክተዋል።

በመሆኑም መኪኖቹ የጫኑት የአፈር ማዳበሪያ በፍጥነት ተራግፎ ለክልሎች እንዲከፋፈል መመሪያ መስጠታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በአስቸኳይ የጫኝ አውራጆችን ቁጥር በመጨመር ማዳበሪያውን በማረጋፍ እንዲሁም በመጋዘን ውስጥ የተከማቸውን ማዳበሪያ ለክልሎች በፍጥነት እንዲከፋፈል ለግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ኃላፊዎች ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

Exit mobile version