አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በ100 ሺህ 414 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የተገነቡ 158 የመስሪያ ሼዶች ተመርቀው በትጋት ለሚሰሩ እጆች ዝግጁ ሆነዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
በሰኔ ወር የተላለፉ 2 ሺህ 389 ሼዶችን ጨምሮ በጥቅሉ በተዘጋጁ ከ2 ሺህ 500 በላይ ሼዶች 17 ሺህ የመዲናዋ ወጣቶችና ሴቶችን እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ብለዋል::
ወጣቶችና ሴቶች በከተማው ባሉ መጠነ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ እራሳቸውን እና ሀገራቸውን መለወጥ እንዲችሉ የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።
ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ሴቶች ጋር በነበራቸው ውይይት ለተጠየቀው የመስሪያ ቦታ ጥያቄ በተጨባጭ ፈጣን ምላሽ እየተሰጠ ነው ሲሉ ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች የሕዝቡን የኑሮ ሸክም የሚያቀልሉ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለሁሉም የምትመች “ውብ አዲስ አበባን” ዕውን ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!