አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኒውዝላንድ እና አውስትራሊያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የሴቶች የዓለም ዋንጫ ወደ ጥሎ ማለፍ የተቀላቀሉ ቡድኖች ተለይተዋል።
በውድድሩ ብራዚል እና ጣሊያን ሳይጠበቅ ከምድባቸው ተሰናብተዋል።
በምድብ 6 ከፈረንሳይ፣ ጃማይካ እና ፓናማ ጋር የተደለደለችው ብራዚል ከምድቡ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ከጥሎ ማለፉ ውጭ ሆናለች።
ከምድብ ሰባት ከስዊድን፣ ደቡብ አፍሪካ እና አርጀንቲና ጋር የተደለደለችው ጣሊያንም በተመሳሳይ ከምድቧ ማለፍ አልቻለችም።
በውድድሩ አፍሪካን ከወከሉ ሀገራት መካከል ናይጀሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ከየምድባቸው በማለፍ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።