አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል አክሱም፣ ዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን ተቀብለዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ግዑሽ (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ተማሪዎቹ የማጠናከሪያ እና የማካካሻ ትምህርት እየተሰጣቸው ነው።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲም በቀጣዮቹ ሶስት ቀናት ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምርም ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በትግራይ ክልል በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰድ ሲገባቸው ያልወሰዱ ተማሪዎች በቀጣይ ፈተና ላይ እንደሚቀመጡ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በክልሉ በቀጣይ መስከረም ወር የመልቀቂያ ፈተና እንደሚሰጥም ትናንት በሰጡት መግለጫ አንስተዋል።