Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አገራቸው ተመለሱ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በኢትዮጵያ የቆዩትን ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ዛሬ ሽኝት አድርገውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷”ውዱ ወንድሜ ሼክ ሙሀመድ ቢን ዛይድ በኢትዮጵያን በነበራቸው ቆይታ በጣም ደስ ብሎኛል” ብለዋል።

“የጋራ የትብብር አድማሳችንን ማስፋት እንቀጥላለን” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version