አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ለመሳተፍ የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ያደረገው ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቶታል።
ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከታንዛኒያው አዛም ጋር የተጫወተው ባህር ዳር ከተማ ጨዋታውን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ፍፁም ጥላሁን የባህር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ጎሎች ሲያስቆጥር ኢድሪስ ሙቦንቦ ደግሞ የአዛንን ጎል አስቆጥሯል።
የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታም በቀጣዩ አርብ በታንዛኒያ ላይ ይደረጋል።