Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አንበጣ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የአውሮፕላን ርጭት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የበረሃ አንበጣ መንጋ በተከሰተባቸው የአማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት መጀመሩን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የእጽዋት ጥበቃ መሪ ሥራ አስፈጻሚ በላይነህ ንጉሴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ አውሮፕላኑ ከኬሚካል ርጭቱ ጎን ለጎን በሰው ሃይል እና በመኪና ለማሰስ አስቸጋሪና ተራራማ በሆኑ ቦታዎች የበረሃ አንበጣ አሰሳ እያደረገ ነው፡፡

የበረሃ አንበጣ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያለው የአየር ንብረት (ከፍተኛ ጉም) አውሮፕላኑ በሚፈለገው ፍጥነት ልክ ሥራውን እንዳያከናውን ማድረጉንም አስታውቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ የአየር ንብረት ሁኔታውን በመቋቋም እስካሁን ተግባሩ መቀጠሉን ነው ያመላከቱት፡፡

በቂ የግብዓት አቅርቦት መኖሩን የገለጹት አቶ በላይ÷ የበረሃ አንበጣውን ሥርጭት በአጭር ጊዜ በቁጥጥ ስር ለማዋል በትጋት እየተሠራ ስለመሆኑ አስረድተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version