አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የአምባሳደሩን መኖሪያ መረቁ።
የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት የመገንባትና የማጠናቀቅ ተሞክሮ ከኢትዮጵያ ውጭም በሚገኙ የመንግስትም ሆነ የግለሰብ ኢትዮጵያውያን ሥራዎች ላይ መንፀባረቅ ያለበት ዕሴት መሆን እንዳለበትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
የመኖሪያ ቤቱ ግንባታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በለውጡ ማግስት በደቡብ አፍሪካ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት የሰጡትን መመሪያ ተከትሎ ነው የተካሄደው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤምባሲው ግቢ ውስጥም የአረንጏዴ ዐሻራ ችግኝ መትከላቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።