Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ግብር ከፋዩ ከአጭበርባሪዎች እራሱን እንዲጠብቅ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከገቢዎች ሚኒስቴር እንደተደወለ በማስመሰል የሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎችን ለመከላከል ግብር ከፋዩ እራሱን እንዲጠብቅ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

“የኦዲት ግኝት አለባችሁ፣ ለሽልማት ታጭታችኋል፣ ድርጅታችሁ ወንጀል መስራቱ ስለተደረሰበት በህግ እንዳትጠየቁ እናደርጋለን” በማለት በስልክ በማስፈራራትና በማደናገር ገንዘብ ለመቀበል የሚጥሩ አካላት ስልቶችን በመቀያየር ግብር ከፋዩን በማጭበርበር ላይ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ስለሆነም በሐሰተኛ ማንነት ከገቢዎች ሚኒስቴር ለድርጅቶች ባለቤት ወይም ሥራ አስኪያጆች በተንቀሳቃሽ ስልክ እንደተደወለ በማስመሰል የሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎችን ለመከላከል ግብር ከፉዩ እና ማህበረሰቡ ከአጭበርባሪዎች እራሱን እንዲጠብቅ ሲል ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

መሰል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም በስልክ ቁጥር 0116-172026 ወይም 0116-172027 ጥቆማ እንዲሰጡ ሲል ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡13:58 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version