ግብር ከፋዩ ከአጭበርባሪዎች እራሱን እንዲጠብቅ ተጠየቀ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
“የኦዲት ግኝት አለባችሁ፣ ለሽልማት ታጭታችኋል፣ ድርጅታችሁ ወንጀል መስራቱ ስለተደረሰበት በህግ እንዳትጠየቁ እናደርጋለን” በማለት በስልክ በማስፈራራትና በማደናገር ገንዘብ ለመቀበል የሚጥሩ አካላት ስልቶችን በመቀያየር ግብር ከፋዩን በማጭበርበር ላይ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ስለሆነም በሐሰተኛ ማንነት ከገቢዎች ሚኒስቴር ለድርጅቶች ባለቤት ወይም ሥራ አስኪያጆች በተንቀሳቃሽ ስልክ እንደተደወለ በማስመሰል የሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎችን ለመከላከል ግብር ከፉዩ እና ማህበረሰቡ ከአጭበርባሪዎች እራሱን እንዲጠብቅ ሲል ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
መሰል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም በስልክ ቁጥር 0116-172026 ወይም 0116-172027 ጥቆማ እንዲሰጡ ሲል ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡13:58