Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለተመድ የሰብዓዊ ድርጅቶች ማብራሪያ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ ድርጅቶች ማብራሪያ ተሰጠ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ በተለይም በአማራ ክልል ስላለው የሰብዓዊ ሁኔታ ለተመድ የሰብዓዊ ድርጅቶች ገለጻ አድርገዋል።

በገለጻቸውም÷ መንግስት አጠቃላይ የሰብዓዊ ሁኔታን ለማሻሻል እና ከዕርዳታ ድርጅቶች ጋር በመሆን አቅርቦት ለማፋጠን ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

አሁን ላይ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አዲስ የክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሾመ እና ክልሉ ወደ ቀድሞ ሁኔታው እየተመለሰ መሆኑንም አስረድተዋል።

በአብዛኞቹ ቦታዎች ተቋርጠው የነበሩ መሠረታዊ አገልግሎቶችም ዳግም መጀመራቸውንም ነው የገለጹት፡፡

አምባሳደር ምሥጋኑ አያይዘውም ÷ የሰብአዊ ዕርዳታ ድርጅቶቹ አፋጣኝ ድጋፍ በሚያሥፈልግባቸው አካባቢዎች ያለውን ሁኔታ በተለይም የምግብ አቅርቦት እና የተለያዩ አሥፈላጊ ድጋፎችን በፍጥነት እንዲከታተሉ ጠይቀዋል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version