አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የደቡብ ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ ሃክ ቼል ሺንን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸውም የኢትዮጵያና የደቡብ ኮሪያ ግንኙነት በይበልጥ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በደም የተሳሰረውን የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያን ግንኙነት በአሁኑ ወቅት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ የገለጹት አቶ ደመቀ÷ በጋራ ጥረት ዘርፈ ብዙ ግንኙነቱን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የደቡብ ኮሪያን የኢኮኖሚ ልማትና የቴክኖሎጂ እድገት እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርትን ከግምት ያስገባ ትብብር እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያን በደቡብ ኮሪያ የትምህርት ተቋማት የመማር ፍላጎት እንዳላቸውም ነው አቶ ደመቀ ያነሱት፡፡
ለደቡብ ኮሪያ በአፍሪካ ካሉ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ጠቅሰው÷ የሀገሪቱ ባለሃብቶች በግብርና፣ በአምራች፣ በማዕድን፣ በቱሪዝምና በኢኖቬሽን መስኮች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በደቡብ ኮሪያ ግዙፍ የኬሚካል ኩባንያ ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው የኤልጂ ኬም ኩባንያ ምክትል ሊቀመንበርና ዋና ስራ አስፈጻሚ ልዩ መልዕክተኛው ሃክ ቼል ሺንን በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።
በተለይም በኢትዮጵያ በመድሃኒት አምራችነትና በግብርና መስክ በኢንቨስትመንት የመሰማራት ፍላጎት እንዳለ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ቁልፍ የሆኑ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ክፍት በማድረግ ለውጭ ኢንቨስተሮች መጋበዟን አድንቀዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!