አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የተከሰተውን የቢጫ ዋግ የመከላከል ስራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው በ6 ሺህ 452 ሔክታር ላይ ቢጫ ዋግ የስንዴ ሰብል በሽታ መከሰቱን ጠቅስ፥ በ4 ሺህ 517 ሔክታሩ ላይ በኬሚካል የታገዘ የመከላከል ሥራ መከናወኑን አስታውቋል።
በሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ጎንደር ዞኖች ሥር በሚገኙ 27 ወረዳዎች በስንዴ ሰብል ላይ ቢጫ ዋግ መከሰቱን የቢሮው የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አግደው ሞላ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በታለ ማሞ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!