አዲስ አበባ ፣ መስከረም 9 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ክሮሺያ ዲፕሎማሲያዊ አጋርነታቸውን የሚኒስትሮች ኮሚሽን በማቋቋም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ተስማሙ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 78ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከክሮሺያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጎርደን ግሪሊች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ ክሮሺያ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ለመክፈት የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ አጋርነትም የሚኒስትሮች ኮሚሽን በማቋቋም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያ በሠላም ግንባታው ረገድ እያደረገች ያለውን ጥረትም አቶ ደመቀ አስረድተዋል፡፡
ከክሮሺያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነትም በይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን አስገንዝበዋል፡፡
እንዲሁም ክሮሺያ ከኢትዮጵያ ጋር ለመሥራትና ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጎርደን ግሪሊች አረጋግጠዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!