Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ታሳታፊዎችን የመምረጥ ሥራ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ተሳታፊ የሚሆኑ የማሕበረሰብ ክፍል ተወካዮችን የማስመረጥ ሂደት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኮሚሽኑ አስተባባሪነት በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ የማሕበረሰብ ክፍል ተወካዮችን የማስመረጥ ሥራ ዛሬ በሁሉም ክፍለ ከተሞች መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

በዚህም በ11 ክፍለ ከተሞች፣ በ119 ወረዳዎች እና በ10 የማሕበረሰብ ክፍሎች 13 ሺህ 90 የየማሕበረሰብ ክፍሉ ተሳታፊዎች መለየታቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version