አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአሜሪካ ሴናተር ማይክ ሮንድስ ከተመራ ልዑክ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሀገራዊ እና ቀጣናዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን የ ”አጎዋ” ተጠቃሚነት ሥምምነት እገዳ እድታነሳም አቶ ደመቀ ጠይቀዋል።
በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በይበልጥ ለማሳደግ የጋራ ፍላጎት መኖሩ በውይይቱ ላይ መንጸባረቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!