Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሆረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሆረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ከተማ ተከበረ ፡፡

በዓሉ “ኢሬቻ የአንድነት እና የወንድማማችነት ዓርማ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቈዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ ከኦሮሚያ ሁሉም ዞኖች የመጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል፡፡

አባገዳዎችና ሃደሲንቄዎች በእጃቸው እርጥብ ሳር በመያዝ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን በማብሰር መልካም ምኞታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በሰላም በመጠናቀቁ ሁሉን ነገር ለፈጠረ አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበትና መጪው ዘመን መልካም  እንዲሆን ፈጣሪን የሚለመንበት በዓል ነው፡፡

በመላኩ ገድፍ

 

Exit mobile version