Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዓድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዝየምን ጨምሮ 7 ፕሮጀክቶች ዘንድሮ ይመረቃሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዝየምን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ የሚገኙ ሠባት ትላልቅ ፕሮጀክቶች በተያዘው በጀት ዓመት እንደሚመረቁ ተመላከተ፡፡

ፕሮጀክቶቹም÷ የዓደዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዝየም፣ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ማስፋፋፊያ ፕሮጀክት፣ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ኤግዚቪሽን የሽርክና ፕሮጀክት፣ አቃቂ ቃሊቲ ተሃድሶ ማዕከል፣ ሰሚት የገበያ ማዕከል፣ ቤቴል የገበያ ማዕከልና የካ 2 የመኪና ማቆሚያ ናቸው።

የፕሮጀክቶቹን ግንባታ በ2016 የበጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ታምሩ ደምሴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የሰሚትና ቤቴል የገበያ ማዕከላት ግንባታ በቅርቡ ተጠናቀው እንደሚመረቁ ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም የዓደዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዝየም ግንባታ ተጠናቆ የዘንድሮው የዓደዋ ድል በዓል እንደሚከበርበት አመላክተዋል፡፡

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version