Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሳይበር ጥቃት ሙከራን በማክሸፍ ከ23 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2015 በጀት ዓመት የተቃጣ የሳይበር ጥቃት ሙከራን በማክሸፍ ከ23 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ከኪሳራ ማዳኑን አስታወቀ።
የ4ኛው የሳይበር ደህንነት ወር አካል የሆነ ጉባኤ “የሳይበር ደህንነት ስጋት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሀም በላይ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ በመርሀ ግብሩ ላይ፤ በቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ በመምጣታቸው የሳይበር ምህዳሩን ለመጠበቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
በዚህም 2015 በጀት ዓመት ተቃጥቶ የነበረ የሳይበር ጥቃትን በማክሸፍ ከ23 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ከኪሳራ ማዳን እንደተቻለም ገልፀዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሀም በላይ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሳይበር ምህዳሩ ቁልፍ የመወዳደሪያ አቅም በመሆኑ የሳይበር ምህዳሩን ደህንነት መጠበቅ የሁሉም ድርሻ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በ2015 በጀት ዓመት 6 ሺህ 959 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸው ተመላክቷል።
የፋይናንስ ተቋማት፣ የፀጥታ እና ደህንነት ተቋማት፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ቁልፍ የመንግስት ተቋማት የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች በስፋት እንደሚደረግባቸውም ነው የተገለጸው፡፡
በፍቅርተ ከበደ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version