Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉባዔ የሚቀርቡ ስድስት ቃልኪዳኖችን አፀደቀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በፈረንጆቹ ታህሳስ 2023 በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉባኤ የሚቀርቡ ስድስት ቃልኪዳኖችን አፀደቀ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ተወካዮች እና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ተወካዮች በተገኙበት ቃል ኪዳኖቹ ላይ አስተያየት ተሰጥቷል።

መድረኩን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ከኢጋድ) ጋር በመተባበር ማዘጋጀቱም ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ከ1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችም ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው መኖር የሚችሉበት የቃል ኪዳን ሰነድ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉባኤ የሚቀርቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ምላሽ፣ የተመረጡ የስደተኛ መለጠለያ ጣቢያዎችን ወደ ከተማነት ማሳደግ፣ የመንግስትን አቅም ማሳደግ፣ ስደተኞችን ብሔራዊ መለያ ህዝብና ቤት ቆጠራ እና አሰራር ውስጥ ማካተት የሚሉት ቃልኪዳኖች በመድረኩ ፀድቀዋል፡፡

ስደተኞች በተጠለሉባቸው አካባቢዎች የግሉን ዘርፍ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ የስደተኞችና ተቀባይ ህብረተሰብን በምግብ ራስ ለማስቻልና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ የመሬትና መስኖ ተጠቃሚነትን ማስፋትና የበይነ መረብ ተደራሽነትን ወደስደተኛ ማዕከላት ማስፋት የሚሉትም እንዲሁ።

በፈቲያ አብደላ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version