Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ የማብሰሪያና ክልሉን የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን ገልጸዋል።
ክልሉ የመልማት እና የማደግ ተስፋውን እውን ለማድረግ ስትራቴጂክ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መግባቱን ያነሱት አቶ አደም፥ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የስራ ኃላፊዎች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የአደረጃጀት ጉዳይን እንደ ግብ በመያዝ አግባብነት የሌላቸው እንቅስቃሴዎች መስተዋላቸውን የጠቆሙት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፥ በዚህም አፍራሽ ተልዕኮ ያላቸው አካላት በሚያደርጉት ጥረት አላስፈላጊ ዋጋ መከፈሉን አብራርተዋል።
ከአደረጃጀት ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን ህገወጥ እንቅስቃሴ ሊታረም እና ሊገራ የሚገባው ጉዳይ እንደሆነ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
አደረጃጀት በራሱ ግብ አይደለም ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ከሀገር እና ህዝብ ዘላቂ ጥቅም አኳያ በጥንቃቄ መምራት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version