አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለቱርክ ሪፐብሊክ 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ለሀገሪቱ መንግስት እና ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፋለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት ÷ ባለፉት ዓመታት ቱርክ ለኢትዮጵያ ላሳየችው ጠንካራ ወዳጅነት እና አጋርነት አድናቆቱን ገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ በቀጣይ ከቱርክ ጋር ያላትን ጠንካራ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጧል፡፡
ለቱርክ ሕዝብና መንግስትም መጪው ጊዜ የሰላም እና የብልጽግና እንዲሆን ተመኝቷል፡፡