Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጋራ ትርክትን ዕውን በማድረጉ ረገድ የም/ቤት አባላት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ የጋራ ትርክትን ዕውን በማድረጉ ረገድ የምክር ቤት አባላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገለጹ፡፡

ለምክር ቤት አባላት በአፍሪካ አመራር ልኅቀት ማዕከል እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና እንደቀጠለ ነው፡፡

አቶ ተስፋዬ በስልጠናው የዛሬ ውሎ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ፅንፍ የወጡ ትርክቶች ስለማይጠቅሙ ሁሉንም በሚያግባባ የጋራ ትርክት መተካት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ብሔራዊ ትርክት በመመስረት ኅብረ ብሔራዊነት፣ አካታችነት፣ ፍትሐዊነትንና ሁሉን አሰባሳቢ ትርክት በማካተት የሀገረ-መንግሥት ግንባታ ሥራችንን ማጠናከር ይኖርብናል ማለታቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የትኛውንም ጽንፍ የወጡ አካሄዶችን በመታገልና በማረም ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን፣ መቻቻልን፣ ሁሉንም ሐይማኖቶች እና ባሕሎችን የሚያስተናግድ የጋራ ትርክት መፍጠር እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

የትርክቶች መነሻ ታሪክ እንደሆነ ጠቁመው÷ ታሪክ ትምሕርት የሚወሰድበት እንጂ የማይመለስና ለማረም ዕድል የሌለው፤ ትርክትን ግን እያረሙና እያስተካከሉ የመሔድን ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ የጋራ ትርክትን ዕውን በማድረጉ ረገድ የምክር ቤት አባላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version