Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አዲስ የተቋቋመውን የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ማዕከል መረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ3 ዓመት በፊት እንዲቋቋም አቅጣጫ ባስቀመጡት መሰረት አዲስ የተቋቋመውን የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ማዕከል ዛሬ መርቀዋል።
ማዕከሉ በተፈጥሮ እና በአደጋ ምክንያት የአካል ጉዳተኛ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በሀገር ውስጥ አጋዥ ቁሶችን ለማምረት እና ለማቅረብ የተቋቋመ ማዕከል ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ማዕከል አጋዥ ቴክኖሎጂዎችን ለማምረት፣ ለማደስ እና ለማቅረብ የተቋቋመ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
እንዲሁም ተደራሽ፣ ጥራት ያለው እና ደንበኛ ተኮር የሰው ሰራሽ እና የአካል ድጋፎች አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል፡፡
Exit mobile version