Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለዘላቂ ሰላም ጉልህ ሚና ያላቸው 72 ሀገር በቀል ዕሴቶች መለየታቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሀገር ግንባታና ለዘላቂ ሰላም ጉልህ ሚና ያላቸው 72 ሀገር በቀል ዋና ዋና ዕሴቶችን በመለየት ሠነድ መዘጋጀቱን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ታዬ ደንደአ እንደገለጹት÷ ሚኒስቴሩ ዕሴቶች ለሀገር ግንባታና ለሰላም መረጋገጥ ያላቸውን ሚና በመረዳት “የማኅበራዊ ሀብት ዴስክ” በማደራጀት እየሠራ ነው፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለግጭት አፈታት የሚጠቅሙ 72 ሀገር በቀል ዋና ዋና ዕሴቶች መለየታቸውን ጠቅሰው÷ ሀገራዊ ዕሴት ላይ የሚያተኩሩ ሠነዶችም መዘጋጀታቸውን ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡

በቀጣይም ሁሉም ማኅብረሰብ ተግባብቶባቸው በተደራጀና ለውጥ በሚያመጣ መልኩ እንደሚተገበሩም አመላክተዋል፡፡

የየትኛውም አካባቢ ዕሴቶች የጋራ ሀገራዊ ሀብት መሆናቸውን ለኅብረተሰቡ ማስገንዘብ እንደሚገባ የገለጹት አቶ ታዬ÷ በዚህ ረገድ ምሁራን፣ ፖለቲከኞችና የሐይማኖት አባቶች የመሪነት ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ቤተሰብም ሥነ- ምግባር ያለው ዜጋን ለመገንባት ዕሴቶችን ለልጆቹ በሚገባ ማስተማር አለበት ነው ያሉት፡፡

መገናኛ ብዙኃንም ዕሴቶች እንዲጎለብቱ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የቀደምት ኢትዮጵያውያን የሕይወት ልምድና ፍልስፍናን የያዙ ዕሴቶች የሚገባቸውን ክብርና ዋጋ አለማግኘታቸው ሀገሪቱ ለበርካታ ችግሮች እንድትጋለጥ ማድረጉንም አንስተዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version