አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳዑዲው ልዑል መሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው የኢትዮጵያን የልማት እና የኢኮኖሚ ሪፎርም ብሎም በቀጠናው እየተጫወተች ያለውን ሚና ጨምሮ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮችን አንስተው መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
ሁለቱ ሀገራት በትብብር ሊሰሩ የሚችሏቸው ብዙ ስትራቴጂያዊ ፍላጎቶች እንዳሏቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
ከዚህ አኳያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ለማቋቋም፣ በሳዑዲ ወገንም የዕዳ አከፋፈልን ሁኔታ በማሻሻል፣ በኃይል አቅርቦት ትብብር ብሎም በልማት ፋይናንስ የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም እንድትደግፍ መግባባት ላይ ተደርሷልም ነው ያሉት።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!